Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ “ወንድሞቻችን በጌታ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሙሴን ተጣሉት፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ ምነው እኛም ያኔ ሞተን ባረፍነው ኖሮ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሙሴ​ንም ተጣ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞ​ትን ኖሮ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ!

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 20:3
13 Referencias Cruzadas  

ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉት። ሙሴም፦ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? ጌታንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።


በቆሬም ምክንያት ከሞቱት ሌላ በመቅሠፍቱ የሞቱት ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።


ሕዝቡም ስለ ደረሰባቸው መከራ በጌታ ላይ አጉረመረሙ፤ ጌታም ሰምቶ እጅግ ተቈጣ፤ የጌታም እሳት በመካከላቸው ነደደ፥ የሰፈሩንም ዳር በላ።


ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።


ጌታም በሰይፍ እንድንሞት ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ለምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”


እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ “እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios