በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን?
ዘፍጥረት 18:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን? |
በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን?
ፍትሕ ማጓደል ወይም ማድላት ወይም ጉቦ መቀበል በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሌሉ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን በመፍራት ትክክለኛ ፍርድ ስጡ።”
እኔም እንዲህ በማለት ጸለይኩ፦ “የሠራዊት አምላክ ሆይ! የሰውን ልብና አእምሮ የምትመረምር አንተ ቅን ፈራጅ ነህ፤ እነሆ ችግሬን ለአንተ አስታወቅሁ፤ ስለዚህም በእነዚህ ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን በቀል እንዳይ አድርገኝ።”
እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?
“እናንተም ‘እንዲህ ከሆነ እግዚአብሔር የሚያደርገው ነገር ትክክል አይደለም’ ትሉ ይሆናል፤ እናንተ እስራኤላውያን እኔን አድምጡ፤ እኔ የማደርገው ነገር ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ ታስባላችሁን? ነገር ግን ትክክል ያልሆነው የእናንተ አካሄድ ነው።
ሙሴና አሮን በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?”
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
“በዚያን ጊዜ እነርሱን እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤ ‘በሕዝባችሁ መካከል የሚነሣውን የጠብና የክርክር አቤቱታ አድምጡ፤ በራሳችሁ ሕዝብ ወይም በእናንተ ውስጥ በሚኖሩት መጻተኞች መካከል ስለሚነሣው ጠብና ክርክር ሁሉ በትክክል ፍረዱ።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።
ስማቸው በሰማይ ወደተጻፈው፥ የቤተ ክርስቲያን የበኲር ልጆች ወደሆኑት ወደ አማኞች ጉባኤ፥ የሁሉ ፈራጅ ወደ ሆነው አምላክና ፍጹምነትን ወዳገኙት የጻድቃን ነፍሳት ቀርባችኋል።
እኔ በበኩሌ ምንም አልበደልኩም፤ በእኔ ላይ ጦርነት በመክፈት ልትበድለኝ የተነሣሣህ አንተ ነህ፤ እንግዲህ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ዛሬ በእስራኤላውያንና በዐሞናውያን መካከል ውሳኔ ይሰጣል።”