ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤
ዘፀአት 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወሩ በገባ እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቋቸው። በዚያ ምሽት ጀምበር ስትጠልቅ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይረዷቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ወር እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ወር እስከ ዐሥራ አራተኛ ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሲመሽ ይረዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት። |
ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤
እኔ እግዚአብሔር ያደረግኹላችሁን ሁሉ በማስታወስ ይህ ቀን መንፈሳዊ ክብረ በዓል ይሁንላችሁ፤ እርሱንም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ እንድታከብሩት ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።”
መላውን የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣሁት በዚህ ቀን ስለ ሆነ ይህን የቂጣ በዓል ትጠብቃላችሁ፤ በሚመጡትም ዘመናት ሁሉ ይህን በዓል ማክበር ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።
መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ።
“እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በዛሬው ምሽት ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ምግብ የሚሆናችሁን ሥጋ ታገኛላችሁ፤ በማለዳም የምትፈልጉትን ያኽል እንጀራ ታገኛላችሁ፤ በዚያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።’ ”
ሁለተኛውንም ጠቦት በምሽት ጊዜ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ በማለዳው መሥዋዕት ባቀረብከውም መጠን ተመሳሳይ ዱቄት፥ ዘይትና ወይን ጠጅ አቅርብ፤ ይህ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የምግብ መባ ነው፤ መዓዛውም እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
“የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ፤ በዚህም በዓል አከባበር እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላላችሁ።
ዘግይተው ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እንዲያከብሩ ተፈቅዶላቸዋል፤ ሲያከብሩም እርሾ የሌለበትን ቂጣ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ።
ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከሕግ መምህራን፥ ከሸንጎውም አባሎች ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ከዚያም በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤