Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያው በመጀመሪያው ቀን ወደ ሲና በረሓ ደረሱ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሦስተኛው ወር እስራኤላውያን ከግብጽ ለቅቀው በወጡበት በዚያችው ዕለት ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሦስተኛውም ወር የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 19:1
16 Referencias Cruzadas  

“ይህ ወር ለእናንተ የዓመቱ መጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ፤


በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።


እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ።


መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ።


እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።


“የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ትከል።


“ስለዚህም ከግብጽ መርቼ ወደ በረሓ አመጣኋቸው፤


እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦


እስራኤላውያንም ጒዞአቸውን በየወገናቸው ቀጥለው ከሲና ምድረ በዳ ወጡ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ዐረፈ።


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፦


ከሬፊዲም ተነሥተው በመጓዝ በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።


“በሲና ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን እንዲህ አለን፦ ‘እነሆ፦ በዚህ ተራራ ላይ ለረጅም ጊዜ ቈይታችኋል፤


እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።


“በሲና ተራራ ከእሳቱ ነበልባል መካከል እግዚአብሔር በአነጋገራችሁ ጊዜ ምንም ያያችሁት መልክ አልነበረም፤


እግዚአብሔር አምላካችን በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳን አደረገ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos