ኤርምያስ 16:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ደግሞ ከአባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አድርጋችኋል፤ እያንዳንዳችሁ እኔን በመታዘዝ ፈንታ የልባችሁን ክፋት ምን ያህል በእልኸኝነት እንደምትከተሉ ተመልከቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ደግሞ ከቀድሞ አባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ሁላችሁም እልኸኞችና ዐመፀኞች ሆናችሁ፤ ለእኔም አትታዘዙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ ፍላጎት ሄዳችኋል፤ እኔንም አልሰማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፥ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ቃሌን ለመስማት እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ሊያገለግሉአቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፥ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማይረባ እንደዚህ መታጠቂያ ይሆናሉ።
በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለምን ተወርውረው ተጣሉ?
ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ አባቶቻችሁ ልማድ ትረክሳላችሁን? ርኩሰታቸውንም ተከትላችሁ ታመነዝራላችሁን?
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዜ ርቃችኋል፥ አልጠበቃችሁትምም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው እንዴት ነው? ብላችኋል።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፥ በልቡ ራሱን በመባረክ፥ ‘ምንም እንኳ እንደ ልቤ ደንዳናነት ብሄድ ሰላም አለኝ’ ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።
መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፥ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።
ዐመፅ እንደ ሟርተኛነት ያለ ኃጢአት፥ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃልና እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”