Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 20:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ አባቶቻችሁ ልማድ ትረክሳላችሁን? ርኩሰታቸውንም ተከትላችሁ ታመነዝራላችሁን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉት ራሳችሁን ታረክሳላችሁን? በረከሱ ምስሎቻቸው ምኞት ትቃጠላላችሁን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እንደ አባቶቻችሁ ራሳችሁን በማርከስና የእነርሱን አጸያፊ ጣዖቶች በማምለክ ለምን ትስታላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ኀጢ​አት ረከ​ሳ​ችሁ፤ አመ​ነ​ዘ​ራ​ችሁ፤ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ው​ንም ተከ​ተ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ አባቶቻችሁ ልማድ ትረክሳላችሁን? ርኵሰታቸውንም ተከትላችሁ ታመነዝራላችሁን?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 20:30
13 Referencias Cruzadas  

እናንተም እንደምታዩት መሣቀቅያ እስኪያደርጋቸው ድረስ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን እንደ በደሉ እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ።


በሥራቸው ረከሱ፥ በድርጊታቸውም አመነዘሩ።


እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም።


ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


ነገር ግን የልባቸውን እልከኝነትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን በኣሊምን ተከትለዋልና


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ፥ ማኅፀን የሚከፍተውን ሁሉ በእሳት ባሳለፉ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።


እኔም፦ እናንተ ወደ እርሱ የምትሄዱበት ከፍታ ምንድነው? አልኋቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠርቶአል።


እነሆም፥ የጌታን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ለመጨመር እናንተ የኃጢአተኞች ትውልድ በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሣችሁ!


እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ፈጽሙ።


“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፥ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos