አሞጽ 2:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕጌን ጥሰዋል፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም፤ አባቶቻቸው ይከተሉአቸው የነበሩት የሐሰት አማልክት እነርሱንም አስተዋቸዋል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ከንቱ ነገር አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ሐሰታቸው አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። Ver Capítulo |