Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወንድሞች ሆይ! ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወዳጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ መካከል ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያርቅ ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከእ​ና​ንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይ​ማ​ኖት የጐ​ደ​ለ​ውና ተጠ​ራ​ጣሪ፥ ከሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ያ​ችሁ ክፉ ልብ አይ​ኑር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 3:12
37 Referencias Cruzadas  

የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ መንገድህን እናውቅ ዘንድ አንወድድም።


እነርሱም እግዚአብሔርን፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።


ጌታ እንደጽድቄ ይከፍለኛል፥ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።


አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


እነርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ ስለዚህ ያዘዝኋቸውን እነርሱም ያላደረጉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ሁሉ አመጣሁባቸው።”


እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ፥ ልቡም ከጌታ የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?


“እነርሱ ግን፦ ‘ተስፋ የለውም! አሳባችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም እንደ ክፉው ልባችን እልከኝነት እናደርጋለን’ አሉ።


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።


በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን የጌታ ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፥ በጌታ ስም አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሷ ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልኸኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም።


ነገር ግን በክፉ ልባቸው ሐሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።


ይህም የእስራኤልን ቤት ለመያዝ ነው፤ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት በልባቸው ከእኔ ተለይተዋልና፤


ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።


ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።


ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ጊዜው ሳይደርስ ሁሉን ነግሬአችኋለሁ።


ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፥ ጸልዩም።


ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።


እንዲህም አለ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች ‘እኔ ነኝ፤ ዘመኑም ቀርቦአል፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።


እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራላቸው ለአንተም አይራራልህምና።


ስለዚህ የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።


እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።


እነርሱ ራሳቸው ስለ እኛ በእናንተ መካከል ምን ዓይነት አቀባበል ተደርጎልን እንደ ነበር፥ ሕያውም የሆነውን እውነተኛ አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ፥


በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።


ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ነፍሴ ወደ ኋላም በሚያፈገፍግ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”


ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥


ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥


የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?


ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ! የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤


ለአርባ ዓመታት፤ ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ “ዘወትር በልባቸው ይስታሉ፤ መንገዴን ግን አላወቁም፤” አልኩ፤


እንግዲህ ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን።


ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos