የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ማስታወቂያዎች


ንዑስ ምድብ

105 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ስለ ወሲባዊ ምስሎች

ወሲባዊ ምኞትን በተሳሳተ መንገድ ማስፈጸምና የብልግና ምስሎች ብዙውን ጊዜ የተያያዙ ናቸው። ብልግና እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ለመላቀቅ ንስሐ መግባት፣ ከኃጢአት መራቅና እግዚአብሔርን መለመን ያስፈልጋል።

ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝ አድርገህ መቀበል በጣም አስፈላጊ ነው። ያለ እርሱ ከብልግና ምስሎች ሱስ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ አስቸጋሪ ነው። በዮሐንስ ወንጌል 15:5 "እኔ የወይኑ ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎቹ ናችሁ። በእኔ የሚኖር፣ እኔም በእርሱ የምኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ግን ምንም ማድረግ አትችሉም" ተብሎ እንደተጻፈ።

በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ኃይል ለተከታዮቹ ይሰጣቸዋል (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3:16)። ይህ ኃይል ውስጣዊ ጥንካሬን ይሰጣል። ለውጥን ለሚፈልጉ ሁሉ የእግዚአብሔር ምሕረትና ይቅርታ ይገኛል። በ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:9 "ኃጢአታችንን ብንናዘዝ፥ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" ተብሎ ተጽፏል።


1 ዮሐንስ 2:16

ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።

ገላትያ 5:16

እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ እላለሁ፤ የሥጋንም ምኞት አትፈጽሙም።

1 ቆሮንቶስ 6:16

ወይስ ከዝሙት ዐዳሪ ጋራ የሚተባበር ሰው ከርሷ ጋራ አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሏልና።

ማቴዎስ 5:28

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከርሷ ጋራ አመንዝሯል።

ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው።

ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ኤፌሶን 5:3

ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና።

1 ቆሮንቶስ 10:13

በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።

1 ቆሮንቶስ 6:18

ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል።

1 ቆሮንቶስ 5:1

በመካከላችሁ የዝሙት ርኩሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኩሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና።

ቲቶ 2:11-12

ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጧልና፤

ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

ሮሜ 8:5-6

እንደ ሥጋ የሚኖሩ ሐሳባቸውን በሥጋ ፍላጎት ላይ ያሳርፋሉ፤ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን ሐሳባቸውን በመንፈስ ፍላጎት ላይ ያደርጋሉ።

የሥጋን ነገር ማሰብ ሞት ነው፤ የመንፈስን ነገር ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

ሐዋርያት ሥራ 15:20

ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኩሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤

ሮሜ 7:24-25

እኔ ምን ዐይነት ጐስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል?

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን! እንግዲያስ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ ባሪያ ስሆን፣ በኀጢአተኛ ተፈጥሮዬ ግን ለኀጢአት ሕግ ባሪያ ነኝ።

1 ተሰሎንቄ 4:3-5

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤

ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤

ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን።

ገላትያ 5:19

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣

2 ቆሮንቶስ 12:21

ዳግመኛም ስመጣ አምላኬ በእናንተ ፊት ያዋርደኝ ይሆን ብዬ እፈራለሁ፤ ይኸውም ብዙዎች ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኀጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፣ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን ነው።

ምሳሌ 6:25-26

ውበቷን በልብህ አትመኝ፤ በዐይኗም አትጠመድ።

ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

መዝሙር 101:3

በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።

ቈላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው።

ሮሜ 12:1-2

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።

እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።

ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ።

በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።

ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።

የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ።

እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋራ ዐብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ።

ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ።

ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ።

ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምሳሌ 4:23

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።

1 ዮሐንስ 2:15-16

ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤

ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።

ዕብራውያን 13:4

ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአመንዝሮችና በሴሰኞች ሁሉ ላይ ይፈርዳል።

ማቴዎስ 5:29-30

ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

“በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

መዝሙር 119:37

ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።

2 ጴጥሮስ 2:10

በተለይም በርኩስ ምኞት የሥጋ ፍላጎታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ ሰማያውያንን ፍጡራን ሲሳደቡ አይፈሩም፤

ምሳሌ 5:3-5

የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ያንጠባጥባልና፤ አንደበቷም ከቅቤ ይለሰልሳል፤

በመጨረሻ ግን እንደ እሬት ትመርራለች፤ ሁለት አፍ እንዳለውም ስል ሰይፍ ትሆናለች።

እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ።

ሮሜ 6:12-13

ስለዚህ ክፉ መሻቱን ትፈጽሙ ዘንድ በሟች ሥጋችሁ ላይ ኀጢአት እንዲነግሥበት አታድርጉ።

ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ገላትያ 6:7-8

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

1 ቆሮንቶስ 3:16-17

እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን?

ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፤ ያም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ።

ኢሳይያስ 33:15

በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣

መዝሙር 119:11

አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

1 ጢሞቴዎስ 6:11

የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።

2 ቆሮንቶስ 10:5

በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

1 ጴጥሮስ 1:14-16

ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ መጠን ቀድሞ ባለማወቅ ትኖሩበት የነበረውን ክፉ ምኞት አትከተሉ።

ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤

ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏል።

ቈላስይስ 2:8

በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ወግና በዚህ ዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

ማቴዎስ 6:22-23

“ዐይን የሰውነት መብራት ነው፤ ስለዚህ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ መላው ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል።

ዐይንህ ታማሚ ከሆነ ግን መላው ሰውነትህ በጨለማ የተሞላ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ድቅድቅ ይሆን?

ምሳሌ 12:15

ቂል ሰው መንገዱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ምክር ይሰማል።

መክብብ 12:1

የጭንቀት ጊዜ ሳይመጣ፣ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ሳይደርሱ፣ በወጣትነትህ ጊዜ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።

መዝሙር 24:3-4

ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?

ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤ በውሸት የማይምል።

መዝሙር 119:9

ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።

ኤፌሶን 4:29

እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ።

ምሳሌ 15:14

አስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይሻል፤ የሞኝ አፍ ግን ቂልነትን ያመነዥካል።

ዕብራውያን 10:24-25

እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።

አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

ሮሜ 8:1

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤

መዝሙር 119:25

ነፍሴ ከዐፈር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

ምሳሌ 7:21-23

በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው።

ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤

ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ።

ማቴዎስ 4:18-19

ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ሁለት ወንድማማቾች ማለትም፣ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን አያቸው። ዓሣ አጥማጆች ነበሩና መረባቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበር።

ኢየሱስም፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ምሳሌ 14:12

ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል።

1 ቆሮንቶስ 15:33

አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”

መዝሙር 37:30-31

የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ አንደበቱም ፍትሓዊ ነገር ያወራል።

የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤ አካሄዱም አይወላገድም።

ሮሜ 12:21

ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

ቈላስይስ 3:2

ሐሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።

1 ዮሐንስ 3:3

በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።

ኢሳይያስ 53:5

ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

2 ጢሞቴዎስ 2:22

ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋራም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።

ሮሜ 1:24-25

ስለዚህም እግዚአብሔር በኀጢአት በተሞላው የልባቸው ምኞት እርስ በርሳቸው የገዛ አካላቸውን እንዲያስነውሩ ቅድስና ለሌለው ሩካቤ ሥጋ አሳልፎ ሰጣቸው።

የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን።

ገላትያ 5:24

የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋራ ሰቅለውታል።

1 ቆሮንቶስ 10:31

እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

ምሳሌ 18:10

የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

ማቴዎስ 26:41

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”

መዝሙር 119:43-44

ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።

ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ።

መዝሙር 26:2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤

ኤፌሶን 5:15-16

እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።

ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ።

ሮሜ 13:14

ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት።

መዝሙር 119:2

ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔር ሕግ፤ ምስክርነቱን የሚጠብቁ፣ በፍጹምም ልብ የሚሹት፤

ምሳሌ 29:11

ሞኝ ሰው ቍጣውን ያለ ገደብ ይለቅቀዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።

2 ቆሮንቶስ 5:17

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል።

ኢሳይያስ 54:17

በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።

ገላትያ 5:13

ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።

መዝሙር 16:8

እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

ፊልጵስዩስ 3:14

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።

ማቴዎስ 7:7-8

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል።

የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

ምሳሌ 16:6

በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።

1 ጢሞቴዎስ 4:12

ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።

ሮሜ 12:3

እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ በሰጣችሁ እምነት መጠን ራሳችሁን በአግባቡ መዝኑ እንጂ፣ ከሆናችሁት በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ እያንዳንዳችሁን እመክራለሁ።

ኤፌሶን 6:12

ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋራ ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋራ ነው።

ምሳሌ 2:10-12

ጥበብ ልብህ ውስጥ ትገባለችና፤ ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤

የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ ማስተዋልም ይጠብቅሃል።

ጥበብ ንግግራቸው ጠማማ ከሆነ ሰዎች፣ ከክፉዎችም መንገድ ታድንሃለች፤

ቈላስይስ 1:10

የምንጸልየውም ለጌታ እንደሚገባ እንድትኖሩና በሁሉም ደስ እንድታሰኙት ነው፤ ይኸውም በመልካም ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ እግዚአብሔርን በማወቅ እያደጋችሁ፣

መዝሙር 119:165

ሕግህን የሚወድዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ ዕንቅፋትም የለባቸውም።

ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

1 ዮሐንስ 1:9

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።

መዝሙር 32:1-2

ብፁዕ ነው፤ መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ ኀጢአቱም የተሸፈነለት፤

የክፉዎች ዋይታ ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን፣ ምሕረት ይከብበዋል።

ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።

ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣ በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት፤

ፊልጵስዩስ 4:13

ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።

ሮሜ 6:14

ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ፣ ኀጢአት አይገዛችሁምና።

ምሳሌ 4:7

ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።

ገላትያ 6:1

ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።

ዕብራውያን 12:1

እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።

ምሳሌ 27:12

አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።

መዝሙር 119:73

እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ።

ኢሳይያስ 26:12

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰላምን መሠረትህልን፤ የሠራነውንም ሁሉ አንተ አከናወንህልን።

ሮሜ 5:3-4

በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን።

ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤

ማቴዎስ 11:28-30

“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።

ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

“ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ።

ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።”

መዝሙር 119:45

ሥርዐትህን እሻለሁና፣ እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ።

1 ቆሮንቶስ 9:27

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ።

ኤፌሶን 4:3

በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።

ገላትያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣

ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።

መዝሙር 119:50

ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣ ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት።

ምሳሌ 6:20-23

ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው።

ምን ጊዜም በልብህ አኑራቸው፤ በዐንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።

በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።

እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤

2 ቆሮንቶስ 10:3-5

የምንኖረው በዚህ ዓለም ቢሆንም፣ የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም።

ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው።

በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

1 ጴጥሮስ 2:11-12

ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።

ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ።

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘላለማዊ አምላክ፥ ልዑል ጌታ! አንተ ጻድቅና ቅዱስ ስለሆንክ፥ ከፍ ያለ ምስጋናና አምልኮ የሚገባህ አንተ ብቻ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ ሕይወቴን የመለወጥና የማደስ ኃይል ያለህ አንተ ብቻ እንደሆንክ አውቄ ወደ አንተ እቀርባለሁ። ከዚህ ርኩስ ሱስ ነፃ እንድትወጣኝ እና መንፈስ ቅዱስህ ሕይወቴን አዲስ አቅጣጫ እንዲሰጠኝና ከዚህ ሱስ እንድርቅ ብርታት እንዲሰጠኝ እለምንሃለሁ። ይህንን የብልግና ሱስና ልማድ ከነፍሴና ከሥጋዬ ነቅለህ እንድታስወግድልኝ እርዳኝ። ጌታ ሆይ፥ ወደዚህ ሱስ የሚገፋፉኝን ሰዎች እንድርቅ አበርታኝ። አእምሮዬን አድስልኝ፤ በቃልህ እንዳስቀመጥከው እቅድ መሠረት እንድኖር ከርኩሰት ሁሉ የጸዳ ሕሊና ስጠኝ። በመንፈስ እንድመላለስና የሥጋን ምኞት እንዳላሟላ አስተምረኝ። ዛሬ አእምሮዬን የሚያረክስና ትዳሬን የሚያፈርስ ብልግና ከመመልከት እንደምቆጠብ ቃል እገባለሁ። በቤቴና በቤተሰቤ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስህ መገኘት ይኑር፤ ምንም ርኩስ ነገር እንዳያረክሰን። ቅዱስ አባት ሆይ፥ ንጹሕ ልብና ቀና መንፈስ ፍጠርልኝ፤ ከዓላማህ ሳልወጣ ወደፊት እንድራመድ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን!