መዝሙር 101 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 101 የዳዊት መዝሙር። 1 ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ። 2 እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ፣ በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ። 3 በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም። 4 ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም። 5 ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣ አጠፋዋለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣ እርሱን አልታገሠውም። 6 ከእኔ ጋራ ይኖሩ ዘንድ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤ በፍጹም መንገድ የሚሄድ፣ እርሱ ያገለግለኛል። 7 አታላይ የሆነ ማንም ሰው፣ በቤቴ ውስጥ አይኖርም፤ ሐሰትን የሚናገር፣ በፊቴ ቀና ብሎ አይቆምም። 8 በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣ በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.