ሶፎንያስ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ ቀን አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ ከእንግዲህ ወዲያ፣ በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞችንና ትምክሕተኞችን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ በእኔ ላይ ስለ ፈጸማችሁት በደል በዚያን ጊዜ አታፍሩበትም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ አትታበዩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም። |
እነርሱም አይጐዱትም፤ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ማንንም አይጐዱም፤ አያጠፉምም፤ ብዙ ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘለዓለማዊ መድኀኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አቷረዱም።”
አታፍሪምና አትፍሪ፤ አቷረጂምና አትደንግጪ፤ የዘለዓለም እፍረትሽንም ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና፥ የሚቃጠለው መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸውም በመሠዊያዬ ላይ የተመረጠ ይሆናል።
“በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው ለዘለዓለም ይገዙልኛል፤ በዚያም እቀበላችኋለሁ፤ በዚያም ቀዳምያታችሁን፥ በኵራታችሁንም፥ የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እጐበኛለሁ።
ለእስራኤል ቤት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኀይላችሁን ትምክሕት፥ የዐይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁንም ምኞት፥ መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
በሙሴና በአሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእናንተ ይበቃችኋል፤ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና፤ በእግዚአብሔርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?” አሉአቸው።
በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
መጽሐፍ እንዲሁ “በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይንና የማሰናከያ ዐለትን አኖራለሁ፤ ያመነባትም ለዘለዓለም አያፍርም” ብሎአልና።