Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 56:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ። የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣ በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “እነርሱን ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አምጥቼ በጸሎት ቤቴም ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ፤ በመሠዊያዬም ላይ የሚያቀርቡትን የሚቃጠልና ሌሎችን መሥዋዕቶች ሁሉ እቀበላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ቤቴ የሕዝቦች ሁሉ ጸሎት ቤት ተብሎ ስለሚጠራ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፥ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 56:7
35 Referencias Cruzadas  

አስተማራቸውም “‘ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“ቤቴ የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላል የሚል ጽሑፍ አለ፤ እና​ንተ ግን የሌ​ቦ​ችና የቀ​ማ​ኞች ዋሻ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት” አላ​ቸው።


“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው።


እኔ ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራው በጽ​ዮን ላይ።


እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


በውኑ እን​ግ​ዲህ በስሙ እና​ምን ዘንድ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን ፍሬ የሚ​ሆን የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን በየ​ጊ​ዜው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልና​ቀ​ርብ አይ​ገ​ባ​ን​ምን?


እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።


በአ​ሮ​ንም ግን​ባር ላይ ይሆ​ናል፤ አሮ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትና በሚ​ቀ​ድ​ሱት በቅ​ዱሱ ስጦ​ታ​ቸው ሁሉ ላይ የሠ​ሩ​ትን ኀጢ​አት ይሸ​ከም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለው እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ቸው ሁል​ጊዜ በግ​ን​ባሩ ላይ ይሁን።


እነ​ር​ሱም አይ​ጐ​ዱ​ትም፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ ላይ ማን​ንም አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፤ ብዙ ውኃ ባሕ​ርን እን​ደ​ሚ​ሸ​ፍን ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወቅ ትሞ​ላ​ለ​ችና።


በዚያ ቀን በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል አን​ዲቱ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ትሆ​ና​ለች፤ በዳ​ር​ቻ​ዋም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ዐ​ምድ ይሆ​ናል።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ።


በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ ቤትም ይከ​ብ​ራል።


በሮ​ች​ሽም ሁል​ጊዜ ይከ​ፈ​ታሉ፤ ሰዎች የአ​ሕ​ዛ​ብን ብል​ጽ​ግና፥ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊ​ትና ቀን አይ​ዘ​ጉም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።


ያን​ጊዜ ተኵ​ላና በግ በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል፤ የእ​ባ​ብም መብል ትቢያ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህ ስሜ የተ​ጠ​ራ​በት ቤት በዐ​ይ​ና​ችሁ የሌ​ቦች ዋሻ ነውን? እነሆ፥ እኔ አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ፥ ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ሁላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​ል​ኛል፤ በዚ​ያም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ በኵ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ የቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ት​ንም ነገር ሁሉ እጐ​በ​ኛ​ለሁ።


ለእ​ና​ን​ተና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ለሚ​ቀ​መጡ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ልጆ​ችን ለሚ​ወ​ልዱ መጻ​ተ​ኞች ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ በዕጣ ትካ​ፈ​ሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እንደ አሉ የሀ​ገር ልጆች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች መካ​ከል ከእ​ና​ንተ ጋር ርስ​ትን ይወ​ር​ሳሉ።


“እኔም በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራዬ በጽ​ዮን የም​ቀ​መጥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​ደ​ሰች ከተማ ትሆ​ና​ለች፥ እን​ግ​ዶ​ችም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ል​ፉ​ባ​ትም።


“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥


በች​ግ​ርሽ ቀን በጮ​ኽሽ ጊዜ እስኪ ይታ​ደ​ጉሽ፤ እነሆ፥ ዐውሎ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ነፋ​ስም ሁሉን ያስ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋል። ወደ እኔ የሚ​ጠጉ ግን ምድ​ሪ​ቱን ይገ​ዛሉ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ።


“እና​ንተ ግን እኔን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ቅዱ​ሱ​ንም ተራ​ራ​ዬን ረሳ​ችሁ፥ ለአ​ጋ​ን​ን​ትም ማዕድ አዘ​ጋ​ጃ​ችሁ፤ ዕድል ለተ​ባለ ጣዖ​ትም የወ​ይን ጠጅ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ቀዳ​ችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios