ሶፎንያስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም ቀድሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ! የጌታ ቀን ቀርቧልና፤ ጌታ መሥዋዕትን አዘጋጅቷል የጠራቸውንም ቀድሶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። |
እኔ አዝዤ ቅዱሳኔን አመጣቸዋለሁ፤ ኀያላኔንም አመጣቸዋለሁ፤ ደስ እያላቸውም ይመጣሉ፤ ቍጣዬንም ይፈጽማሉ፤ ያዋርዱአቸዋልም።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የአምላካችን የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ በልቶ ይጠግባል፤ በደማቸውም ይሰክራል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መሥዋዕት በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነውና።
“እነሆ ቀኑ ደርሶአል፤ እነሆ! የእግዚአብሔር ቀን ወጥታለች፤ ስብራትህ ደርሶአል፤ ብትርም አብባለች፤ ስድብም በዝቶአል።
እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የምታስፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገለጣለች፥ መጠኗ ምንድን ነው? ማንስ ይችላታል?
አጥንቶቻቸውንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተሰቦቻቸው በወሰዱአቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባቂውን በአንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእግዚአብሔርንም ስም እንዳትጠራ ዝም በል ይለዋል።
ያንጊዜም በመቅደሶቻቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በየስፍራው የሚወድቀው ሬሳ ይበዛልና፤ እነርሱም ይጠፋሉና።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
እርሱም፥ “ለሰላም ነው፤ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፤ ቅዱሳን ሁኑ፤ ከእኔም ጋር ዛሬ ደስ ይበላችሁ፤ ከእኔም ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ” አለ። እሴይንና ልጆቹንም ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።
ሳኦልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆናል፤ ምንአልባትም ንጹሕ አይደለም ይሆናል፤ በእውነትም ንጹሕ አይደለም” ብሎ አስቦአልና በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።