Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በሀ​ገር የም​ት​ኖር ሆይ! ስብ​ራ​ትህ ጊዜው ደረሰ፤ ቀኑም ቀረበ፤ የሽ​ብር ቀን ነው እንጂ የተ​ራራ ላይ ዕል​ልታ አይ​ደ​ለም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እናንተ በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሷል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቧል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በምድር የምትኖር ሆይ፥ ፍጻሜህ ወደ አንተ መጥቷል፥ ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሽብር ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በምድሪቱ የምትኖሩ ሕዝብ ሁሉ የመጥፊያችሁ ጊዜ ደርሶአል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ እርሱም የሁከት ቀን ነው እንጂ በከፍተኛ ቦታዎች የመፈንጠዣ ቀን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በምድር የምትቀመጥ ሆይ፥ ተራህ ደርሶአል፥ ጊዜ መጥቶአል፥ ቀን ቀርቦአል፥ የሽብር ቀን ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 7:7
16 Referencias Cruzadas  

ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ መላ​እ​ክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስ​ት​ህ​ንና ከዚህ ያሉ​ትን ሁለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ች​ህን ውሰድ፤ አን​ተም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ጠፋ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤


ተኵ​ላ​ዎ​ችም በዚያ ያድ​ራሉ፤ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም በሚ​ያ​ማ​ምሩ አዳ​ራ​ሾ​ቻ​ቸው ይዋ​ለ​ዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆ​ናል፤ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።


ደስ​ታና ሐሤ​ትም ከወ​ይን ቦታሽ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ በወ​ይ​ን​ሽም ቦታ​ዎች ፈጽ​መው ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም፤ በመ​ጥ​መ​ቂ​ያ​ውም ወይ​ንን አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ረጋ​ጮ​ቹን አጥ​ፍ​ቻ​ለ​ሁና።


በመ​ሸም ጊዜ ሳይ​ነጋ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ያን​ጊ​ዜም የይ​ሁዳ ወገ​ኖች “ይህ የወ​ራ​ሾች ርስት ነው፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​ንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።


ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሁ​ከ​ትና የጥ​ፋት፥ የመ​ረ​ገ​ጥና የስ​ብ​ራ​ትም ቀን በጽ​ዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖ​አል። ታና​ሹና ታላ​ቁም ሸሽ​ተው በተ​ራራ ላይ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ።


አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል።


ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው!


ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል።


ጊዜው መጥ​ቶ​አል፤ ቀኑ እነሆ ቀር​ቦ​አል፤ መቅ​ሠ​ፍቷ በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ መል​ቶ​አ​ልና የሚ​ገዛ ደስ አይ​በ​ለው፤ የሚ​ሸ​ጥም አይ​ዘን።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እር​ሱም በጥ​ፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመ​ጣል።


እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos