Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዩኤል 2:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፤ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 2:31
21 Referencias Cruzadas  

“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ፀሐ​ይና ጨረቃ ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።


ምድ​ሪ​ቱም ከፊ​ታ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ሰማ​ይም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ፀሐ​ይና ጨረ​ቃም ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።


“በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ።


“እነ​ሆም በዚያ ወራ​ትና በዚያ ዘመን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


የም​ት​ገ​ለ​ጠው ታላ​ቅዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።


አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።


ስለ​ዚህ ምድር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በላ​ይም ሰማይ ይጠ​ቍ​ራል፤ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፤ አል​ጸ​ጸ​ትም ወደ​ፊት እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም አል​መ​ለ​ስም።


በጠ​ፋ​ህም ጊዜ ሰማ​ዮ​ችን እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ ፀሐ​ዩ​ንም በደ​መና እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ጨረ​ቃም ብር​ሃ​ኑን አይ​ሰ​ጥም።


በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በቅ​ዱ​ሱም ተራ​ራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይደ​ን​ግጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን መጥ​ቶ​አ​ልና፥ እር​ሱም ቀር​ቦ​አ​ልና።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios