ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
ሮሜ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሥጋ ዘመዶችና ወንድሞች ስለሚሆኑ እኔ ከክርስቶስ እለይ ዘንድ እጸልያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድድ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ሥጋ ዘመዶቼና ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ ከክርስቶስ ተለይቼ የተረገምሁ እንድሆን እመኝ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑት ወገኖቼ ስል እኔ ከክርስቶስ ተለይቼ የእግዚአብሔር ርግማን ቢደርስብኝ በወደድኩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና። |
ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
“እናንተ ከአብርሃም ወገን የተወለዳችሁ ወንድሞቻችን እግዚአብሔርንም የምትፈሩ፥ ይህ የሕይወት ቃል ለእናንተ ተልኮአል።
እንዲቀጡም ከዚያ ያሉትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ወደ አሉ ወንድሞች እንድሄድ ከእነርሱ ዘንድ የሥልጣን ደብዳቤ የተቀበልኋቸው ሊቀ ካህናቱና መምህራን ሁሉ ይመሰክራሉ።
የአይሁድ ታላላቅ ሰዎችም እንዲህ አሉት፥ “ለእኛስ ከይሁዳ ሀገር ስለ አንተ መልእክት አልደረሰንም፤ ከኢየሩሳሌም ከመጡት ወንድሞችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስቀድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወራን፥ የነገረንም የለም።
እንግዲህ እላለሁ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? አይደለም፤ እኔ ደግሞ ከአብርሃም ዘር ከብንያም ወገን የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ።
ከዘመዶች ወገን የሚሆን ሄሮድዮናን ሰላም በሉ፤ በንርቃሶስ ቤት ያሉትንና በክርስቶስ ያመኑትን ምእመናን ሰላም በሉ።
ከእኔ ጋር በሥራ የሚተባበረው ጢሞቴዎስም፥ ከዘመዶች ወገን የሚሆኑ ሉቅዮስም፥ ኢያሶንም፥ ሱሲ ጴጥሮስም ሰላም ይሉአችኋል።
ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል።
ስለዚህም ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ “ኢየሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው” ሊል አንድስ እንኳን እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወጣለሁ፤ ስለ ሕይወታችሁም ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እናንተንም እጅግ ብወዳችሁ ራሴን ወደድሁ።
እናንተ ግን የእኛን ፍለጋ ተከተሉ፤ እናንተስ እኛም ብንሆን ወይም መልአክ ከሰማይ ወርዶ እኛ ካስተማርናችሁ ወንጌል ሌላ ቢሰብክላችሁ ውጉዝ ይሁን።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”
አገልጋዮችም በሥጋችሁ ለሚገዙአችሁ ጌቶቻችሁ በፍርሀትና በመደንገጥ፥ በሰፊ ልብም ለክርስቶስ እንደምትገዙ ታዘዙ።
በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሥጋው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።
ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም።