እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት።
እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ማመስገንና የምስጋና መዝሙር ለአንተ ማቅረብ መልካም ነው።
ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤ አመሰግናለሁ እዘምራለሁም።
ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ። ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።
በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ አልሁ፥
የኤዶምያስ ወገኖች፥ እስማኤላውያንም፥ ሞዓባውያንም፥ አጋራውያንም፥
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
መዝሙርንና ምስጋናን፥ የተቀደሰ ማሕሌትንም አንብቡ፤ በልባችሁም ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ዘምሩም።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?
እንኪያስ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚገቡበት ጸንቶ የሚኖር ዕረፍት እንዳለ ታወቀ።