መዝሙር 81:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤ በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሉ ለሙሉ ግብጽን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣ ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት። በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው። ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤ |
እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ ሀገር አልፋለሁ፤ በግብፅም ሀገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ በቀልን አደርግባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
‘ይህ በግብፅ ሀገር የእስራኤልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብፃውያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን የአዳነ የእግዚአብሔር የፋሲካው መሥዋዕት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጐነበሱ፤ ሰገዱም።
እንዲህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምርኮኛ በኵር ድረስ፥ በግብፅ ምድር በኵሩን ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵር ሁሉ መታ።
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ኀያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋንቋቸውንም የማታውቀው፥ የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሁኑ።