እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
መዝሙር 79:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ በባሪያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣ በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ፥ በዙሪያችን ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ ሆነናል። |
እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ አገልጋዩም አሞናዊው ጦቢያ፥ ዓረባዊውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድን ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ፈጽሞ ምድረ በዳ ይሆኑ ዘንድ፥ ለርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፥ ነገሥታቷንም፥ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።
ስድባችንን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ ቤተ መቅደሳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ከድኖታል።
ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እንጀራ አጥተው ያለቅሳሉ፤ ሰውነታቸውን ለማበርታት ፍላጎታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፤ አቤቱ! ተጐሳቍያለሁና እይ፤ ተመልከትም።
አንተም፦ ፈርሰዋል፤ መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ።
ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አትሸከሚም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።