ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቶ፥ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።
መዝሙር 72:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜው ይርዘም! ወርቅም ከሳባ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት፤ ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐወት ይኑር፥ ከዓረብም ወርቅ ይሰጠው፥ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልይ፥ ዘወትርም ይባረክ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር! ከሳባ ወርቅ ይምጣለት፤ ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረግ፤ የእግዚአብሔርም በረከት ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሁን! |
ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቶ፥ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።
የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንግዲህ ወዲህም ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።