Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 72 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ስለ ሰሎሞን።

2 አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥ ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።

3 በጽድቅ፥ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።

4 ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ይፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች ያድን፥ ጨቋኙንም ይጨፍልቅ።

5 ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።

6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይውረድ።

7 በዘመኑም ጽድቅ ያብብ፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ይብዛ።

8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይግዛ።

9 በፊቱም የኢትዮጵያ ሰዎች ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።

10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፥ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።

11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።

12 ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።

13 ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።

14 ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፥ ደማቸው በፊቱ ክቡር ነው።

15 በሐወት ይኑር፥ ከዓረብም ወርቅ ይሰጠው፥ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልይ፥ ዘወትርም ይባረክ።

16 በምድር ላይ እህሉ ይትረፍረፍ፥ በተራሮችም ላይ ሰብል ይወዛወዝ፥ ፍሬውም እንደ ሊባኖስ ከፍ ከፍ ይበል፥ ሰዎችም በከተማ እንደ ምድር ሣር ይለምልሙ።

17 ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥ እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥

18 ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።

19 የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። አሜን፥ አሜን።

20 የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎቶች ተፈጸሙ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos