መዝሙር 64:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አንተ የሚመጣ የሰውን ሁሉ ጸሎት ስማ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክፉዎች አድማ ሰውረኝ፤ ከዐመፀኞችም ሸንጎ ጋርደኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በሮሮዬ ድምፄን ስማ፥ ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ። |
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
አንተ ግን አቤቱ! ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውንም ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፤ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።”
ልኮም ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ እንዲያስመጣውና እንዲሰጣቸው ለመኑት፤ እነርሱ ግን ወደዚያ ሄደው በመንገድ ሸምቀው ሊገድሉት ፈልገው ነበር።