አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
ነፍሴም እጅግ ታወከች፥ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
እግዚአብሔር ሆይ! ተመልሰህ ታደገኝ፤ የዘለዓለም ፍቅርህን በማሳየት አድነኝ።
ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
በኀይልህ ሰላም ይሁን፥ በክብርህ ቦታ ደስታ አለ።
የሚያስተውል፥ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
እግዚአብሔርም በሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
የኃጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ። የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤
በተኵላና በእባብ ላይ ትጫናለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
ሰውነቴንም እንዳትጠፋ ይቅር አልሃት፤ ኀጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላዬ ጣልህ።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።
በሚወደው ልጁ የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ።