Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 74 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ አታ​ጥፋ የአ​ሳፍ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።

1 አቤቱ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ ስም​ህ​ንም እጠ​ራ​ለሁ፤ ተአ​ም​ራ​ት​ህን ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።

2 ጊዜ​ውን ባገ​ኘሁ ጊዜ እኔ በቅን እፈ​ር​ዳ​ለሁ።

3 ምድ​ርና በእ​ር​ስዋ ውስጥ የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋን አጸ​ናሁ።

4 ኃጥ​ኣ​ንን አል​ኋ​ቸው፥ “አት​በ​ድሉ” የሚ​በ​ድ​ሉ​ት​ንም አል​ኋ​ቸው፥ “ቀን​ዳ​ች​ሁን አታ​ንሡ፥

5 ቀን​ዳ​ች​ሁን እስከ አር​ያም አታ​ንሡ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን አት​ና​ገሩ።”

6 ክብር ከም​ሥ​ራቅ ወይም ከም​ዕ​ራብ ወይም ከም​ድረ በዳ የለ​ምና፤

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋ​ር​ዳል ይህ​ንም ያከ​ብ​ራል።

8 ጽዋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነውና፤ ያል​ተ​ቀ​ላ​ቀለ የወ​ይን ጠጅ ሞላ​በት፤ ከዚህ ወደ​ዚህ አቃ​ዳው፥ ነገር ግን አተ​ላው አል​ፈ​ሰ​ሰም፤ የም​ድር ኃጥ​ኣን ሁሉ ይጠ​ጡ​ታል።

9 እኔ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ ይለ​ኛል፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እዘ​ም​ራ​ለሁ፥

10 የኃ​ጥ​ኣ​ንን ቀን​ዶች ሁሉ እሰ​ብ​ራ​ለሁ። የጻ​ድ​ቃን ቀን​ዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos