Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ሆይ! ተመልሰህ ታደገኝ፤ የዘለዓለም ፍቅርህን በማሳየት አድነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነፍሴም እጅግ ታወከች፥ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አቤቱ፥ ተመ​ለስ ነፍ​ሴ​ንም አድ​ናት፥ ስለ ቸር​ነ​ት​ህም አድ​ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 6:4
20 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ሕይወቴን ከክፉዎች አድን።


ከቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሕጌ ርቃችኋል፤ አልጠበቃችሁትምም። ‘ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’፥ እናንተ ግን ‘ወደ አንተ የምንመለሰው በምን ዐይነት ነው?’ ትላላችሁ።


እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ሕይወትህንም በሰላም ይጠብቃል።


በዚያን ጊዜ “አምላክ ሆይ! እባክህ አድነኝ!” ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ።


እግዚአብሔር ሆይ! ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል? እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ!


የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ! ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤ ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ!


ነፍሴን ከሰይፍና ከእነዚያ ውሾች ኀይል አድነኝ።


ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው።


ችግር የደረሰብኝ በእርግጥ ለደኅንነቴ ነው፤ ከአደጋም ሁሉ ሕይወቴን ታድናለህ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር ትላለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ከሐሰተኞችና ከአታላዮች አድነኝ።


እግዚአብሔር ከሞት አዳነኝ፤ እንባዬ እንዲቆም አደረገ፤ እግሮቼንም ከመደናቀፍ ጠበቃቸው።


ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።


አምላክ ሆይ! እንደ ቸርነትህ በዘለዓለማዊ ፍቅርህ አስበኝ እንጂ የወጣትነት ኃጢአቴን ወይም በደሌን አታስብብኝ!


ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል? እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል? እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?


አምላክ ሆይ! ጠላቶች በአንተ ላይ የሚሳለቁት እስከ መቼ ነው? ስምህንስ የሚዳፈሩት ያለማቋረጥ ነውን?


እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios