ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጣለህ፥ ዕድል ፋንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
በሕይወት ሳለ ራሱን እንደ ተባረከ ቢቈጥርም፣ ሰዎች በበለጸግህ ጊዜ ቢያወድሱህም፣
በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።
ሰው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ቢደሰትና ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም እንኳ
ወይም ወርቅን ካበዙ፥ ቤታቸውንም ብር ከሞሉ አለቆች ጋር፥
አንተ የሠራኸውን እነሆ፥ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ?
ያችም ባለጠግነት በክፉ ንጥቂያ ትጠፋለች፤ ልጅንም ቢወልድ በእጁ ምንም የለውም።
በከነዓን እጅ የዐመፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚያንም ይወድዳል።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
“የዚህንም ርግማን ቃሎች በሰማችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስንፍና በማድረግ ሄጃለሁና ይቅር ይለኛል’ የሚል ቢኖር የበደለኛ ፍዳ ካልበደለ ጋር እንዳይተካከል፥
እንዲህም በሉት፥ “ደኅንነትና ሰላም ለአንተና ለቤትህ፥ ለአንተም ለሆኑት ሁሉ ይሁን።