Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በከ​ነ​ዓን እጅ የዐ​መፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚ​ያ​ንም ይወ​ድ​ዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤ “እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከከነዓን ወገን ነው፤ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ‘እስራኤል እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤ በሀብቴም ማንም ሰው በእኔ ላይ በደል ወይም ኃጢአት አያገኝብኝም’ ብሎ ይፎክራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከከነዓን ወገን ነው፥ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 12:8
29 Referencias Cruzadas  

‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥


በሰ​ይፍ እጅ አል​ፈው ይሰጡ፥ የቀ​በ​ሮ​ዎ​ችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።


የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ ራሳቸውንም እንደ በደለኞች አድርገው አይቈጥሩም፣ የሸጡአቸውም፦ ባለ ጠጋ ሆነዋልና እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ፣ እረኞቻቸውም አይራሩላቸውም።


ሰማ​ያት ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና።


በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ እን​ዳ​ትል።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


ለሁ​ለት ጌቶች መገ​ዛት የሚ​ችል አገ​ል​ጋይ የለም፤ ካል​ሆ​ነም አን​ዱን ይወ​ድ​ዳል፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይጠ​ላል፤ ወይም ለአ​ንዱ ይታ​ዘ​ዛል፤ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም እንቢ ይላል፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ገን​ዘብ እየ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መገ​ዛት አት​ች​ሉም።”


ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ።


ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።


ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል።


እድል ፈንታው በእነርሱ ሰብታለችና፥ መብሉም በዝቶአልና ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል።


አን​ቺስ፦ አል​ረ​ከ​ስ​ሁም፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አል​ተ​ከ​ተ​ል​ሁም፤ እን​ዴት ትያ​ለሽ? በሸ​ለቆ ያለ​ውን መን​ገ​ድ​ሽን ተመ​ል​ከቺ፤ ያደ​ረ​ግ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመ​ን​ገ​ዶች ትጮ​ኻ​ለች፤


አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።


እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።


በታ​ላቅ ጥበ​ብ​ህና በን​ግ​ድህ ብል​ጽ​ግ​ና​ህን አብ​ዝ​ተ​ሃል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ና​ህም ልብህ ኰር​ቶ​አል።


ሕዝ​ቤ​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም በበ​ደ​ላ​ቸው ይወ​ስ​ዷ​ታል።


ከተ​ሰ​ማ​ራ​ችሁ በኋላ ጠገ​ባ​ችሁ፤ በጠ​ገ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ልባ​ችሁ ታበየ፤ ስለ​ዚ​ህም ረሳ​ች​ሁኝ።


ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።


ቀፎ ወፎ​ችን እን​ደ​ሚ​ሞላ፥ እን​ዲሁ ቤታ​ቸው ሽን​ገ​ላን ሞል​ታ​ለች፤ በዚ​ህም ከብ​ረ​ዋል ባለ​ጸ​ጎ​ችም ሆነ​ዋል።


“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios