መዝሙር 49:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዱር አራዊት ሁሉ፥ የምድረ በዳ እንስሶችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባን ሟቾች መሆናቸው የሚታይ ነው፤ ሞኝና ደነዝም ይጠፋሉ፤ ጥሪታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም እንደሚያውቀው ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሰነፎች እኩል ይሞታሉ፤ ሁሉም ሀብታቸውን ትተው ይሄዳሉ። |
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።