አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ።
የዳዊት ጸሎት። አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ተንኰል ከሌለበት ከንፈር የሚወጣውንም ጸሎቴን አድምጥ።
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።
በእርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆናለሁ፤ ከዐመፃዬም ራሴን እጠብቃለሁ።
አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖች ይገለጣሉ፤ ጆሮዎችም ያዳምጣሉ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።
ሆዴ በልቅሶ ተቃጠለ፤ የሞት ጥላን በቅንድቦች ላይ አያለሁ፤
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
ልቤ በላዬ ደነገጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም መጣብኝ።
ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
እርሱ አምላኬ መድኀኒቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነው ሁልጊዜም አልታወክም።
እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ ይፈርዳል፤ አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው።
መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤
እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ፥
ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
በዚህም ሁሉ ከዳተኛዪቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም” ይላል እግዚአብሔር።
‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
ናትናኤልም፥ “በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን?” አለው፤ ፊልጶስም፥ “መጥተህ እይ” አለው።
ወዳጆች ሆይ፥ ልባችንስ ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፥