Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 84:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ክብር በም​ድ​ራ​ችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚ​ፈ​ሩት ቅርብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አምላክ ሆይ፤ ጋሻችንን እይልን፤ የቀባኸውንም ተመልከት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤ ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 84:9
16 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


የዳ​ዊ​ትም የመ​ጨ​ረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ገው፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ የቀ​ባው፥ የታ​ማኙ ሰው፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መል​ካም ባለ​መ​ዝ​ሙር የሆ​ነው፥ የታ​ማኙ የእ​ሴይ ልጅ የዳ​ዊት ንግ​ግር ይህ ነው፤


አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ከቀ​ባ​ኸው ሰው ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ለባ​ሪ​ያ​ህም ለዳ​ዊት ምሕ​ረ​ትን አስብ።”


አቤቱ፥ በኀ​ይሌ እወ​ድ​ድ​ሃ​ለሁ።


የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተነሡ፥ አለ​ቆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ እን​ዲህ ሲሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።


እኔ ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራው በጽ​ዮን ላይ።


አንተ ግን አቤቱ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ክብ​ሬና ራሴን ከፍ ከፍ የም​ታ​ደ​ር​ገው አንተ ነህ።


በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።


ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት።


በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤል​ያብ ተመ​ል​ክቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ባው በፊቱ ነው” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቹን ያደ​ክ​ማ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበ​በኛ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ሀብ​ታ​ምም በሀ​ብቱ አይ​መካ፤ የሚ​መካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወ​ቅና በማ​ስ​ተ​ዋል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል ፍር​ድ​ንና እው​ነ​ትን በማ​ድ​ረግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አን​ጐ​ደ​ጐ​ደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈ​ር​ዳል፤ ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንም ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ የመ​ሲ​ሑ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos