Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዮሐንስ 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ወዳጆች ሆይ፥ ልባችንስ ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ወዳጆች ሆይ፤ ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ወዳጆች ሆይ፥ ልባችን የማይወቅሰን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ወዳጆች ሆይ፥ ልባችን የማይወቅሰን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ መተማመን ይኖረናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ወዳጆች ሆይ፥ ልባችንስ ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፥

Ver Capítulo Copiar




1 ዮሐንስ 3:21
17 Referencias Cruzadas  

አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።


በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።


በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን ታገ​ኛ​ለህ። ወደ ሰማ​ይም በደ​ስታ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ።


የሚ​ያ​ጠ​ራ​ጥ​ረ​ኝና ትዝ የሚ​ለኝ ነገር የለም፤ በዚ​ህም ራሴን አላ​መ​ጻ​ድ​ቅም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ልና።


ጽድ​ቅን እየ​ሠ​ራሁ አል​ጠ​ፋም፤ ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር አይ​ታ​ወ​ቀ​ኝ​ምና።


እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።


እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።


እኛ ጸጋ​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ በሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ​ሚ​ገ​ኘው ተስ​ፋም ያደ​ረ​ሰ​በት፤


ወንድሞች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረቻችሁ አሮጌ ትእዛዝ እንጂ የምጽፍላችሁ አዲስ ትእዛዝ አይደለችም፤ አሮጌይቱ ትእዛዝ የሰማችኋት ቃል ናት።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios