ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
መዝሙር 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ ሐዘናቸው ይበዛል፤ እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሌላ አምላክ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል፥ የቁርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም፥ ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም። |
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
በሸለቆ ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች ዕድል ፋንታሽ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?
“እናንተ ግን እኔን ተዋችሁኝ፤ ቅዱሱንም ተራራዬን ረሳችሁ፥ ለአጋንንትም ማዕድ አዘጋጃችሁ፤ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ቀዳችሁ፤
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
የስንዴም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ይሁን፤ የመጠጡም ቍርባን የወይን ጠጅ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ ይሁን።
በእናንተም መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክቶቻቸውም ስሞች በእናንተ መካከል አይጠሩ፤ አትማሉባቸውም፤ አታምልኳቸውም፤ አትስገዱላቸውም፤