መዝሙር 148:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማየ ሰማያት፥ ከሰማያት በላይ ያለ ውኃም ያመሰግኑታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥ ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፍተኞች ሰማያት አመስግኑት፤ ከጠፈር በላይ ያላችሁ ውሃዎችም አመስግኑት። |
በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
ዕዝራም እንዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጥረሃል፤ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።
በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ዘመኑ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ነጥቀው ወሰዱት።