Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥ በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኖኅ 600 ዓመት በሆነው ጊዜ፥ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ውሃ ምንጮች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፤ በሰማይ ያሉት የውሃ መስኮቶች ሁሉ ተከፈቱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 7:11
27 Referencias Cruzadas  

የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ድም​ፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰ​ማይ ይታ​ወ​ካሉ፤ ከም​ድ​ርም ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ና​ብም ጊዜ መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።


በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።


ያም ሎሌ ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ወ​ርድ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” ብሎ ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፥ ከዚ​ያም አት​ቀ​ም​ስም” ብሎት ነበር።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰው እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ባድማ ከተማ ባደ​ረ​ግ​ሁሽ ጊዜ፥ ቀላ​ዩ​ንም ባወ​ጣ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆ​ችም በከ​ደ​ኑሽ ጊዜ፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በሚ​ፈ​ሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰ​ፍ​ራል፥ ያድ​ና​ቸ​ው​ማል።


ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠፈ​ርን አደ​ረገ፤ ከጠ​ፈር በላ​ይና ከጠ​ፈር በታች ያሉ​ት​ንም ውኆች ለየ።


በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥


ምድር ደነ​ገ​ጠች፤ ታወ​ከ​ችም፤ ምድር ጐሰ​ቈ​ለች፤ ተነ​ዋ​ወ​ጠ​ችም።


እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል።


በአ​ፈር ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ከ​ፈል ወንዝ የጽ​ድ​ቅን መን​ገድ የረሱ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ። ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል ይለ​ያሉ።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውሃ ሰጥሞ ጠፋ፤


ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።


እነሆ፥ ዝና​ብን ከሰ​ማይ ቢከ​ለ​ክል ምድ​ርን ያደ​ር​ቃ​ታል፤ እን​ደ​ገና ቢተ​ዋ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለ​ችም።


ወደ ባሕር ምን​ጭስ ውስጥ ገብ​ተ​ሃ​ልን? በጥ​ል​ቁስ መሠ​ረት ውስጥ ተመ​ላ​ል​ሰ​ሃ​ልን


በዕውቀቱ ቀላያት መነጩ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።


የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፍ​ተ​ዋ​ልና፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ከፍ​ር​ሀት ድምፅ የሸሸ በገ​ደል ይወ​ድ​ቃል፤ ከገ​ደ​ልም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ምድር ደረ​ቀች።


የሰ​ማ​ይን ደመና በጥ​በቡ ሊቈ​ጥር የሚ​ችል ማን ነው? ሰማ​ይ​ንም ወደ ምድር ያዘ​ነ​በለ ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios