Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 113 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሃሌ ሉያ።

1 እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም ወገን ከጠ​ላት ሕዝብ በወጡ ጊዜ፥

2 ይሁዳ መመ​ስ​ገ​ኛው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ግዛቱ ሆነ።

3 ባሕር አየች፥ ሸሸ​ችም፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ወደ​ኋ​ላው ተመ​ለሰ።

4 ተራ​ሮች እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ዘለሉ።

5 አንቺ ባሕር የሸ​ሸሽ፥ አን​ተም ዮር​ዳ​ኖስ ወደ ኋላህ የተ​መ​ለ​ስህ፥ ምን ሁና​ችሁ ነው?

6 እና​ን​ተም ተራ​ሮች፥ እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችስ፥ እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ለምን ዘለ​ላ​ችሁ?

7 ከያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ፊት፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምድር ተና​ወ​ጠች፤

8 ዐለ​ቱን ወደ ውኃ ምንጭ፥ ባል​ጭ​ቱ​ንም ወደ ውኃ ኩሬ የለ​ወጠ።

9 ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ

10 አሕ​ዛብ፥ “አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው?” አይ​በሉ።

11 አም​ላ​ካ​ች​ንስ በላይ በሰ​ማይ ነው፤ በሰ​ማ​ይም በም​ድ​ርም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀ​ደ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።

12 የአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታ​ቶች የወ​ር​ቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።

13 አፍ አላ​ቸው ግን አይ​ና​ገ​ሩም፤ ዐይን አላ​ቸው ግን አያ​ዩም፤

14 ጆሮ አላ​ቸው ግን አይ​ሰ​ሙም፤ አፍ​ንጫ አላ​ቸው ግን አያ​ሸ​ት​ቱም፤

15 እጅ አላ​ቸው ግን አይ​ዳ​ስ​ሱም፤ እግር አላ​ቸው ግን አይ​ሄ​ዱም፤ በጉ​ሮ​ሮ​አ​ቸ​ውም አይ​ና​ገ​ሩም።

16 በአ​ፋ​ቸው ትን​ፋሽ የለም፥ የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ም​ኑ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ እነ​ርሱ ይሁኑ።

17 የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።

18 የአ​ሮን ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤ ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አስ​በን ባር​ከ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች ባርክ፥ የአ​ሮ​ን​ንም ወገ​ኖች ባርክ።

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን፥ ትን​ን​ሾ​ች​ንና ትል​ል​ቆ​ችን ሁሉ ባር​ካ​ቸው።

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ያ​ችሁ፥ በላ​ያ​ች​ሁና በል​ጆ​ቻ​ችሁ ላይ ይጨ​ምር።

23 እና​ንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለሠራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ናችሁ።

24 የሰ​ማ​ዮች ሰማይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ግን ለሰው ልጆች ሰጠ።

25 አቤቱ፥ ሙታን የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉም፥ ወደ ሲኦ​ልም የሚ​ወ​ርዱ ሁሉ፤

26 እኛ ሕያ​ዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos