በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
ምሳሌ 24:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጻድቅ ሰው ቤት ላይ እንደ ወንበዴ አታድፍጥ፤ መኖሪያውንም በድንገት አታጥቃ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ክፉ ሰው በጻድቅ ቤት ላይ አትሸምቅ፥ ማደሪያውንም አታውክ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ዐመፀኛ ሰው የጻድቁን ሰው ቤት ለመዝረፍ አትሸምቅ፤ መኖሪያውንም አትውረር። |
በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
ልኮም ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ እንዲያስመጣውና እንዲሰጣቸው ለመኑት፤ እነርሱ ግን ወደዚያ ሄደው በመንገድ ሸምቀው ሊገድሉት ፈልገው ነበር።
ሳውል ግን በእርሱ ላይ ሊያደርጉት የሚሹትን ዐወቀባቸው፤ ሊገድሉትም በቀንና በሌሊት የከተማውን በር ይጠብቁ ነበር።