Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 32:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቤም በሰ​ላም ከተማ ይኖ​ራል። ተዘ​ል​ሎም በው​ስ​ጥዋ ያድ​ራል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ናም ያር​ፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣ በሚያስተማምን ቤት፣ ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፥ በታመነ ቤት፥ በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ይሆናሉ፤ ቤቶቻቸውም በሰላምና በደኅንነት የተሞሉ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 32:18
26 Referencias Cruzadas  

እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው።


እን​ኪ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ የሚ​ገ​ቡ​በት ጸንቶ የሚ​ኖር ዕረ​ፍት እን​ዳለ ታወቀ።


እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋል፤ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ማረሻ፥ ጦራ​ቸ​ው​ንም ማጭድ ለማ​ድ​ረግ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ሕዝ​ብም በሕ​ዝብ ላይ ሰይ​ፍን አያ​ነ​ሣም፤ ሰል​ፍ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ማ​ሩም።


በዚ​ያም ቀን የእ​ሴይ ሥር ይቆ​ማል፤ የተ​ሾ​መ​ውም የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ይሆ​ናል፤ አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሱ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ ማረ​ፊ​ያ​ውም የተ​ከ​በረ ይሆ​ናል።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኀ​ዘ​ን​ህና ከመ​ከ​ራህ፥ ከተ​ገ​ዛ​ህ​ለ​ትም ከጽኑ ባር​ነት ያሳ​ር​ፍ​ሃል።


በአ​ንተ ላይ ታም​ና​ለ​ችና በአ​ንተ የም​ት​ደ​ገፍ ነፍ​ስን ፈጽ​መህ በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ታ​ለህ።


አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሁሉን ሰጥ​ተ​ኸ​ና​ልና ሰላ​ምን ስጠን።


እር​ሱም፥ “ይህ​ችም ለደ​ከመ ዕረ​ፍት ናት፤ ይህ​ችም መቅ​ሠ​ፍት ናት፤” አላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ብት​ጸ​ጸ​ትና ብታ​ለ​ቅስ ትድ​ና​ለህ፤ የት እን​ዳ​ለ​ህም ታው​ቃ​ለህ፤ በከ​ንቱ ታም​ነ​ሃ​ልና፤ ኀይ​ላ​ች​ሁም ከንቱ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አላ​ችሁ፤


የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ።


ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ማል፤ ወይ​ኑን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተቀ​ም​ጠው በነ​በ​ሩ​ባት በጌ​ሤም ሀገር ብቻ በረዶ አል​ወ​ረ​ደም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፥ ደስ ይለ​ኛል፥ ሰቂ​ማ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥ የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።


ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥


በድ​ኅ​ነ​ታ​ችን መዝ​ገብ በሕግ ይሰ​በ​ስ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥበ​ብና ምክር፥ ጽድ​ቅም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የጽ​ድቅ መዝ​ገ​ቦች ናቸው።


እን​ግ​ዲህ ለአ​ሕ​ዛብ ንጥ​ቂያ አይ​ሆ​ኑም፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት አይ​በ​ሉ​አ​ቸ​ዋም፤ ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጣሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios