La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል፤ አልባሌ ሰዎችን አያገለግልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሥራው ብልህ ሰው ትመለከታለህን? በነገሥታት ፊት ያገለግላል፥ በተራ ሰዎችም ፊት ሊያገለግል አይቆምም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሥራው የሠለጠነ ሰው ታያለህን? እንደዚህ ያለ ሰው በተራ ሰው ፊት ሳይሆን በነገሥታት ፊት ለአገልግሎት ይቆማል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 22:29
19 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ያለ​በ​ትን እን​ደ​ዚህ ያለ ሰውን እና​ገ​ኛ​ለን?”


ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ።


በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”


አሣ​ሄ​ል​ንም አን​ሥ​ተው በቤተ ልሔም በአ​ባቱ መቃ​ብር ቀበ​ሩት፤ ኢዮ​አ​ብና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በሩ ሰዎ​ቹም ሌሊ​ቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬ​ብ​ሮ​ንም አነጉ።


ሚስ​ቶ​ችህ የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆሙ፥ ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንም ጐል​ማ​ሳው ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሥራ የጸና መሆ​ኑን ባየ ጊዜ በዮ​ሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው።


እነ​ዚህ በነ​ጣ​ዔ​ምና በጋ​ዲራ ከን​ጉሡ ጋር የሚ​ቀ​መጡ ሸክላ ሠራ​ተ​ኞች ነበሩ። እነ​ር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ጸን​ተው በዚያ ይኖሩ ነበር።


የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።


የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤ ሐሰተኞች ሰዎች ግን ለምርኮ ይሆናሉ።


በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤


ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊ​ቱም ቆመ፤ እጅ​ግም ወደ​ደው፤ ለእ​ር​ሱም ጋሻ ጃግ​ሬው ሆነ።


ዳዊ​ትም የተ​ና​ገ​ረው ቃል ተሰማ፤ ለሳ​ኦ​ልም ነገ​ሩት፤ ወደ እር​ሱም ወሰ​ደው።