ምሳሌ 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅ መንሻ ለሰጪው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤ በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቁ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች ጉቦ እንደ አስማት የሚሠራ ይመስላቸዋል፤ ጉቦ በመስጠትም ሁሉ ነገር ይሳካልናል ብለው ያምናሉ። |
አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና።
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፥ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃልሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊትሽንም እንዳከበርሁ ተመልከቺ” አላት።