አብድዩ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተሰነጠቀም ዓለት ውስጥ እንደሚኖር- ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ፥ በልቡም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል፥ የልብህ ትዕቢት እጅግ አኵርቶሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤ በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤ የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤ ‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል። |
እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላንም በጦርነት ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት።
የይሁዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ማረኩ። ወደ ዐለቱም ራስ ላይ አመጡአቸው፤ ከዐለቱም ራስ ላይ ጣሉአቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።
የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
በንግድህም ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ፤ ኀጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ! ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።