La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ በመ​ካ​ከሉ የማ​ድ​ር​በ​ትን ሰፈ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ከወ​ንድ እስከ ሴት ከሰ​ፈሩ አው​ጡ​አ​ቸው።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈር አስወጧቸው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመካከላቸው እኔ የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ፥ እነዚህን ያልነጹ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከመካከላችሁ ወጥተው እንዲባረሩ አድርጉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው።

Ver Capítulo



ዘኍል 5:3
23 Referencias Cruzadas  

በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ በነ​በሩ አግ​ዳ​ሚ​ዎች ቤቱ በዋ​ንዛ ሳንቃ ተሸ​ፍኖ ነበር፤ አዕ​ማ​ዱም በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት፥ በአ​ንዱ ወገን ዐሥራ አም​ስት የሆኑ አርባ አም​ስት ነበሩ።


ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


መቅ​ደስ ትሠ​ራ​ል​ኛ​ለህ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አድ​ራ​ለሁ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


“እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።


በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእ​ና​ንተ ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ማኅ​በሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነውና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታ​በ​ያ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።


ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”


እና​ንተ በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር የማ​ድ​ር​ባ​ትን ምድር አታ​ር​ክ​ሱ​ኣት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የማ​ድር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ከሰ​ፈሩ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተና​ገ​ረው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ድ​ንህ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጥህ በሰ​ፈ​ርህ ውስጥ ይሄ​ዳ​ልና ስለ​ዚህ ነው​ረኛ ነገር እን​ዳ​ያ​ይ​ብህ፥ ፊቱ​ንም ከአ​ንተ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ ሰፈ​ርህ የተ​ቀ​ደሰ ይሁን።


“ከጌ​ታዉ ኰብ​ልሎ ወደ አንተ የተ​ጠ​ጋ​ውን ባሪያ ለጌ​ታው አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ።


ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኀጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤