La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 29:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱም ምንም ሥራ አትሠሩበትም፤ በዚያን ቀን መለከት ይነፋል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው።

Ver Capítulo



ዘኍል 29:1
21 Referencias Cruzadas  

እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ ጀመሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ግን ገና አል​ተ​መ​ሠ​ረ​ተም ነበር።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።


ካህ​ኑም ዕዝራ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሕጉን በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ጉባኤ፥ አስ​ተ​ው​ለ​ውም በሚ​ሰ​ሙት ሁሉ ፊት አመ​ጣው።


ለድ​ሆ​ችና ለድሃ አደ​ጎች ፍረዱ፤ ለተ​ገ​ፋ​ውና ለም​ስ​ኪኑ ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤


መከ​ራን ባሳ​የ​ኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉ​ንም ባየ​ን​ባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለ​ናል።


በፊቴ ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። በእ​ር​ሻም የም​ት​ዘ​ራ​ትን የፍ​ሬ​ህን በኵ​ራት የመ​ከር በዓል፥ ዓመ​ቱም ሲያ​ልቅ ፍሬ​ህን ከእ​ርሻ ባከ​ማ​ቸህ ጊዜ የመ​ክ​ተ​ቻ​ውን በዓል ጠብቅ።


የሰ​ባ​ቱ​ንም ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እር​ሱም የስ​ንዴ መከር መጀ​መ​ሪያ ነው፤ በዓ​መ​ቱም መካ​ከል የመ​ክ​ተቻ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ታላቅ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ በአ​ሦ​ርም የጠፉ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም የተ​ሰ​ደዱ ይመ​ጣሉ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


መጀ​መ​ሪ​ያ​ይቱ ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።


እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።


“በበ​ዓለ ሠዊት ቀን በሰ​ን​በ​ታት በዓ​ላ​ችሁ አዲ​ሱን የእ​ህል ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የተ​ቀ​ደሰ ቀን ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።


“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል አድ​ርጉ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦ​ቶች፥


“ስም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ በዓል ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።