በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥”
ዘኍል 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በርሱም ቃል ይገባሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በጌታ ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበሩም ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ። |
በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥”
በፍርዱ ልብሰ እንግድዓም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
ልብሰ እንግድዓውንም በእርሱ ላይ አደረገ፤ በልብሰ እንግድዓውም ላይ የምልክትና የእውነት መገለጫዎችን አኖረበት።
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
በፊታቸው የሚወጣውንና የሚገባውን፥ የሚያስወጣቸውንና፥ የሚያስገባቸውንም፥ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን።”
በምስክሩም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር፥ በአለቆቹም፥ በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦
አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ በፊትህ ያልፋል፤ እርሱ እነዚህን አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ ትወርሳቸውማለህ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ኢያሱ በፊትህ ይሄዳል።
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመከራም ለፈተኑት፥ በክርክር ውኃም ለሰደቡት፥ ለእውነተኛው ሰው ጽድቁን መልስ።
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፥ “ከነዓናውያንን የሚወጋልን ማን አለቃ ይወጣልናል?” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጠየቁ።
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ።
ሳኦልም ከካህኑ ጋር ሲነጋገር በፍልስጥኤማውያን መንደር ግርግርታ እየበዛ ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን፥ “እጅህን መልስ” አለው።
ዳዊትም ሳኦል በእርሱ ለክፋት ዝም እንደማይል ዐወቀ፤ ዳዊትም ካህኑን አብያታርን፥ “የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣ” አለው።
ሳኦልም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም በሕልም አላሚዎች፥ ወይም በነጋሪዎች፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።
ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አቅርብልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አቀረበለት።