ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
ዘኍል 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በለዓምን፥ “ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትርገም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን በለዓምን፣ “ዐብረሃቸው አትሂድ፤ የተባረከ ሕዝብ ስለ ሆነም አትርገመው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በለዓምን፦ “ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትረግምም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በለዓምን “ከነዚህ ሰዎች ጋር አትሂድ፤ የተባረኩ ስለ ሆነ የእስራኤልን ሕዝብ አትርገም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በለዓምን፦ ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትረግምም አለው። |
ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ “ሕዝቡ መባውን ወደ እግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፤ ጠጥተናልም፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ ከዚህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተናገረ።
ዘራቸው በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ያውቃል፤
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።
እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያዬም ተቀምጦአል፤ ምናልባት እወጋው፥ አሳድደውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁንም ና እርሱን ርገምልኝ።”
በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፥ “ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደልኝምና ወደ ጌታችሁ ሂዱ” አላቸው።
እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል፤ አሁንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበልጣልና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የመረቅኸው ምሩቅ፥ የረገምኸውም ርጉም እንደ ሆነ አውቃለሁና” ብሎ ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ።
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
በለዓምም ባላቅን፥ “በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግዚአብሔር ቢገለጥልኝ፥ ቢገናኘኝም እሄዳለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ቃል እነግርሃለሁ” አለው። ባላቅም በመሠዊያው ዘንድ ቆመ፤ በለዓም ግን እግዚአብሔርን ይጠይቅ ዘንድ አቅንቶ ሄደ።
አርፎአል፥ እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤ የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን ይሰማ ዘንድ አልወደደም፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ወድዶሃልና ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠልህ።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”
ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ ከሴቶችህ መካን አትኖርም፤ ልጆች የሌሏት አገልጋይም አትኖርም፤ ከከብትህም መካን አይኖርም።