Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ የም​ድ​ርን ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ዬም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ ምና​ል​ባት እወ​ጋው፥ አሳ​ድ​ደ​ውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁ​ንም ና እር​ሱን ርገ​ም​ልኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድሩን ገጽ አጥለቅልቆታል፤ ስለዚህ መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባት ልዋጋቸውና ላባርራቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ‘እነሆ፥ ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፥ ምናልባት ልወጋው ላሳድደውም እችል እንደሆነ አሁን ና እርሱን ርገምልኝ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ ምድሪቱን ሸፍኖአታል፤ መጥተህ ብትረግምልኝ ምናልባት እነርሱን በጦርነት ተዋግቼ ላስወጣቸው እችል ይሆናል።’ ”

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 22:11
8 Referencias Cruzadas  

አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


በለ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ ልኮ​አ​ቸ​ዋል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር አት​ሂድ፤ የተ​ባ​ረከ ነውና ሕዝ​ቡን አት​ር​ገም” አለው።


ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኽ​ብኝ ምን​ድን ነው? ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ፤ እነ​ሆም፥ መባ​ረ​ክን ባረ​ክ​ሃ​ቸው” አለው።


በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ባላቅ ከም​ሥ​ራቅ ተራ​ሮች፤ ከሜ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ ጠርቶ አመ​ጣኝ፤ ና፥ ያዕ​ቆ​ብን ርገ​ም​ልኝ፤ ና፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ተጣ​ላ​ልኝ” ብሎ።


ባላ​ቅም በበ​ለ​ዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆ​ቹ​ንም አጨ​በ​ጨበ፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፦ ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግም ዘንድ ጠራ​ሁህ፥


እኔ ግን ላጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ መባ​ረ​ክ​ንም ባረ​ክ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ጁም አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos