La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራ​ብም ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ ሞዓብ ሜዳ ተጕዘው ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከኢያሪኮ ማዶ ሰፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በዮርዳኖስ ማዶ ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ጒዞአቸውን በመቀጠል ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅና በኢያሪኮ ትይዩ በሚገኘው በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በዮርዳኖስ ማዶ ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ።

Ver Capítulo



ዘኍል 22:1
14 Referencias Cruzadas  

በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ።


ከባ​ሞ​ትም ምድረ በዳ​ውን ከላይ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞ​ዓብ በረሃ ወዳ​ለው ወደ ያኒን ሸለቆ ተጓዙ።


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦


የማ​ረ​ኩ​ትን ምር​ኮ​ው​ንና የዘ​ረ​ፉ​ትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ወዳ​ለው ሰፈር አመጡ።


ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወዲህ ወደ ምሥ​ራቅ ርስ​ታ​ችን ደር​ሶ​ና​ልና እኛ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ​ዚያ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ርስት አን​ወ​ር​ስም።”


እነ​ዚህ ሁለቱ ነገ​ድና የአ​ንዱ ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወረሱ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ያዘ​ዛ​ቸው ትእ​ዛዝ፥ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ እነ​ዚህ ናቸው።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ምድር ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ይህን ሕግ ይገ​ልጥ ጀመር፦


“በዚ​ያም ዘመን ከአ​ር​ኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤር​ሞን ድረስ ምድ​ሪ​ቱን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከነ​በሩ ከሁ​ለቱ ከአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥ​ታት እጅ ወሰ​ድን፤


ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።