ዘኍል 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሖርም ተራራ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የኤዶምንም ምድር ዞሩአት፤ ሕዝቡም በመንገድ ተበሳጩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሖርም ተራራ የኤዶምያስን ምድር በዙርያው አድርገው ለመሄድ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ ሕዝቡም በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ ጉልበታቸው ደከመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሖርም ተራራ ከኤዶምያስ ምድር ርቀው ሊዞሩ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የሕዝቡም ሰውነት ከመንገዱ የተነሣ ደከመ። |
ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ፥ ከሥራቸውም ክብደት የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም።
ዐማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆ ውስጥ ተቀምጠዋል፤ እናንተ ግን ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።”
ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድሪቱንም አዩአት፤ እግዚአብሔርም ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ መለሱ።
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።
“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።
እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፤ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ፤ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና ወደ ሞዓብ ድንበር አልገቡም።