እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
ዘኍል 19:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳም የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን፥ ወይም የሰውን አጥንት፥ ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሜዳ ላይ በሰይፍ የተገደለውን ወይም እንዲሁ የሞተውን ወይም ደግሞ ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የገደለውን ወይም በሕመም የሞተውን ሰው በውጭ ወድቆ ሳለ ሬሳውን የሚነካ ሰው፥ ወይም የሰው ዐፅም፥ ወይም መቃብር የሚነካ ሰው ለሰባት ቀን የረከሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳም በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን አጥንት ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፥ “ከወገናቸው በሞተ ሰው ራሳቸውን እንዳያረክሱ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው።
እናንተም ከሰፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገደለ ሁሉ፥ የተገደለውንም የዳሰሰ ሁሉ፥ እናንተና የማረካችኋቸውም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጉ።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ሰዎች ሳያውቁ በላዩ እንደሚመላለሱበት እንደ ተሰወረ መቃብር ናችሁና።”