Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ስለ ሞተው ራሱን አያርክስ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከሕዝቡ መካከል የሞተውን ሰው አስከሬን በመንካት ስለ ሞተ ሰው ማናቸውም ራሳቸውን እንዳያረክሱ የአሮን ተወላጆች ለሆኑ ካህናት ንገራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለው፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ ስለ ሞተው፥

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 21:1
12 Referencias Cruzadas  

እን​ዳ​ይ​ረ​ክ​ሱም ወደ ሞተ ሰው አይ​ግቡ፤ ነገር ግን ለአ​ባት፥ ወይም ለእ​ናት፥ ወይም ለወ​ንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወ​ን​ድም፥ ወይም ላል​ተ​ዳ​ረች እኅት ይር​ከሱ።


ካህ​ናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! አድ​ምጡ፤ የን​ጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድ​ርጉ፤ ለሚ​መ​ለ​ከት ወጥ​መድ፥ በታ​ቦ​ርም ላይ የተ​ዘ​ረጋ አሽ​ክላ ሆና​ች​ኋ​ልና ፍርድ በእ​ና​ንተ ላይ ነው።


ሰው ቢሞት ምላጭ ወደ ሥጋ​ችሁ አታ​ቅ​ርቡ፤ ገላ​ች​ሁ​ንም አት​ን​ቀ​ሱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይ​ግባ፤ በአ​ባ​ቱም ወይም በእ​ናቱ አይ​ር​ከስ።


አሁንም እናንተ ካህናት ሆይ፥ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።


ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


“ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚ​ገባ ሁሉ በቤ​ቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለም​ጻ​ሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገ​ርም ያለ​በ​ትን ሁሉ በሰ​ው​ነቱ የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ከሰ​ፈሩ እን​ዲ​ያ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው፤


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይ​ቅ​ረብ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos