ዘኍል 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለሌዊም ልጆች እነሆ፥ በምስክሩ ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በመገናኛው ድንኳን በሚያገለግሉበት ጊዜ ለሚሠሩት ሥራ ደመወዝ እንዲሆናቸው ከእስራኤል የሚወጣውን ዐሥራት ሁሉ ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ የሚያመጡትን ዐሥራት ሁሉ የሌዋውያን ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ይህም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ደመወዝ ይሆንላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ። |
በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባችሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”
ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደረጋት።
መባኡንና ዐሥራቱን፥ የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡ። ሌዋዊውም ኮክንያስ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
ሌዋውያኑም ዐሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን ዐሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ።
እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።
ለሌዋውያን፥ ለመዘምራንና ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ዐሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን ቀዳምያቱን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘጋጅቶለት ነበር።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ያደርጉ ዘንድ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው።
ከእነዚያም ከተዋጉት፥ ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር ታወጣላችሁ።
ከሌዊ ልጆችም፥ ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ ከእነርሱ ዐሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው።